Skip to main content
የኢትዮጵያ ሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ ተጀመረ
ሆሳዕና ፣ ጥር 2፣ 2017 የኢትዮጵያ ሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ በዛሬው ዕለት ተጀምሯል፡፡
 
በማስጀመሪያ መርሐ ግብሩ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ ÷ለኢኮኖሚና ፋይናንስ ምህዳራችን ታሪካዊ በሆነ እጥፋት የኢትዮጵያን የመጀመሪያ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ ደወል ደውልናል ብለዋል።
ፈጣን የኢኮኖሚ እድገት ባላት፣ ለብልጽግና ሰፊ እምቅ አቅምና ምቹ መንገድ እየተነጠፈላት ባለችው ኢትዮጵያ ባለሃብቶች መዋዕለ ንዋያቸውን እንዲያፈሱም ጥሪ አቅርበዋል፡፡
Read More
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ሃላፊ ዶክተር ዲላሞ ኦቶሬ ለገና በዓል ያስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ፦

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ሃላፊ ዶክተር ዲላሞ ኦቶሬ ለገና በዓል ያስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ፦

በቅድሚያ ለክልላችንና ለአገራችን የክርስትና ዕምነት ተከታዮች  እንኳን ለጌታችንና ለመድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል/ገና/ በሰላምና በጤና አደረሳችሁ አደረሰን!! በዓሉ የደስታ፣ የሰላም፣ የጤና፣የፍቅርና የአንድነት እንዲሆንልን! እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ!!በክርስትና ዕምነት ተከታዮች ዘንድ ከሚከበሩ ትላልቅ አውደ ዓመቶች አንዱና ትልቁ የገና በዓል ነው። በዓሉ ከሀይማኖታዊ ክንዋኔው ባለፈ የተለያዩ ባህላዊ መስተጋብሮች የሚከወንበት ፣አብሮነትና መተጋገዝ ፣ሰላምና ፍቅር ፣ደስታና ብሩህ ተስፋ በጥምረት የሚንጸባረቁበት ነው።በተለይም በዕለቱ በተለያዩ አካባቢዎች ወጣቶች የሚያደርጓቸው የገና ጨዋታዎች ፣አብሮ መብላት፣መጠያየቅ፣ፍቅርና ደስታው የበዓሉ አይረሴዎች ናቸው።በዓሉን ስናከብር በክልሉ የተጀመረውን ሁሉ አቀፍ የብልጽግና ጉዞ ለማስቀጠል ቃላችንን የምናድስበት፣በአፈጻጸም ያገኘናቸውን ስኬቶች ለማላቅና ያጋጠሙ ጉድለቶችን በጋራ ለማረም ቃል የምንገባበት መሆን ይኖርበታል። በክልላችንና በአገራችን የፈነጠቀው የብልፅግና ብሩህ ተስፋ ቀጣይ እንዲሆን፣የተጀመረው ድህነትን ከመሰረቱ የመናድ ራዕይ እንዲሰምር፣የህዝባችንን ዘላቂ ተጠቃሚነትና ክብር የማረጋገጥ ስራዎች ይበልጥ ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ማድረግ ያስፈልጋል።

በየአካባቢያችን የተጀመሩ የብልፅግና ጉዞ ማሳለጫ ጥረቶችን በአዲስ እሳቤና ብሩህ ተስፋ ማስቀጠል ፣ባህል እንዲሆኑ መስራት፣ሰላምን ማረጋገጥና ማጽናት ተገቢ መሆኑንም መገንዘብ ያስፈልጋል።የዘንድሮውን የገና በዓል በአብሮነትና በመረዳዳት፣በፍቅር፣ በመተጋገዝ፣ በመተሳሰብና ብሩህ ተስፋን ተጎናጽፈን እናክብረው።በዓሉን ስናከብር በሰው ተኮር እሳቤ የተቸገሩትን በማገዝ፣ የታረዙትን በማልበስ፣አቅመ ደካሞችን በመደገፍ፣ጧሪ የሌላቸው ወገኖችንና ህጻናትን በመደገፍና በመንከባከብ ማዕዳችንን በማጋራት ልናከብር ይገባል።በዓሉ በሁሉም መስክ ያስመዘገብናቸውን ስኬቶች ፣ቱሩፋቶችና ወረቶች ወደ ባህልና ወደዘላቂ ተግባራት የምንቀይርበት፣በክልሉ የተገኙ ስኬቶችን ለማላቅና የህዝባችንን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ትልቅ ተስፋ የምንሰንቅበት ይሆን ዘንድ እመኛለሁ።በአጠቃላይም ለክልላችንና ለአገራችን ህዝቦች በዓሉ የሰላምና የጤና እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ!ለፓርቲያችን አባላትና ደጋፊዎች በድጋሚ መልካም የገና በዓል!!

Read More
ዶ/ር ዲላሞ ኦቶሬ በፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ህልፈተ ህይወት የተሰማቸውን ሀዘን ገለጹ

የማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ቅርጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊና የመንግስት ዋና ተጠሪ ዶ/ር ዲላሞ ኦቶሬ በፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ህልፈተ ህይወት የተሰማቸውን ሀዘን ገለጹ

/ ዲላሞ ኦቶሬ ባስተላለፉት የሀዘን መግለጫ መልዕክት ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ በኢትዮጵያ የሰላማዊ ፖለቲካ ትግል ተምሳሌት የሆኑ ናቸው ብለዋል።

እስከ ህልፈተ ህይወታቸው ያላቸውን ሁሉ ለአገራቸው በመስጠት አገልግለዋል።

በህልፈተ ህይወታቸው የተሰማኝን ጥልቅ ሃዘን ልገልጽ እወዳለሁ ብለዋል።

/ ዲላሞ ኦቶሬ ለቤተሰቦቻቸውና ወዳጅ ዘመዶቻቸው ለመላው ኢትዮጵያውያን መጽናናትን ተመኝተዋል።

Read More