Party Message
ዶ/ር ዲላሞ ኦቶሬ የማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ቅርጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊና የመንግስት ዋና ተጠሪ
![]() | |||
የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ አጭር መልዕክት ![]() የማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊና ምክትል የመንግስት ተጠሪ ዘርፋችን የክልሉን ሁለንተናዊ የብልጽግና ጉዞ በማሳለጥ ክልላችን የብልጽግና እና የተሞክሮ ማዕከል እንዲሆን ይሠራል፡፡ ከአዲስ ምዕራፍ፣ በወል እሴት ወደ መስፈንጠ ር ከፍታ ብለን የጀመርነው ክልላዊ ጉዞ እውን እንዲሆን የሚያስችሉ የፖለቲካና የንቅናቄ ሥራዎች በስኬት እንዲተገበሩ ያስተባብራል፡፡ ክልላዊ ሁለንተናዊ ሁኔታን በመዳሰስ፣ የንቅናቄ ሥራዎችን በማስተባበር፣ የአመራርና አባላት አቅም በመገንባት እና የፓርቲያችን እሳቤዎችና ገዥ ትርክት የመገንባት ትልማችን እውን እንዲሆን ጠንክሮ ይሠራል፡፡ በአጠቃላይ ጠንካራ የፓርቲ ተቋም በመገንባት፣ ጠንካራ መንግስት እና ሀገረ መንግስት በመገንባት ሂደት የክልሉ ህዝቦች ግንባር ቀደም ተዋናይ እና ባለቤት እንዲሆኑ በማድረግ ሠላማዊና የተረጋጋ ክልል በመገንባት የብልጽግና ህልምና ጉዞ እውን እንዲሆን አበክሮ ይሠራል፡፡ | የአደረጃጀት ዘርፍ አጭር መልዕክት ![]() የማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልል ብልፅግና ፓርቲ አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊና ምክትል የመንግስት ተጠሪ ብልፅግና ፓርቲ በሀሳብ ትልቅነት ግዙፍ አባላትና ብዙ አመራር ያሰባሰበ እና የሚመራበት የአሰራር ስርዓት ያሉት ፓርቲ ነው፡፡ የፓርቲው ህልሙም በመደመር መንገድ መዳረሻው ሁለንተናዊ ብልፅግና በኢትዮጵያ በማረጋገጥ ለአፍሪካ ተምሳሌት መሆን ነው፡፡ ይህንን ታላቅ ሀሳብ ለማሳካት በተደራጀና ተዓማኒነት ባለው መረጃ ግዙፉ አባላትና አመራር በተደራጀ መንገድ መምራት ሲቻል ነው፡፡ ስለሆነም እንደ ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልልም የብልፅግና ህልሙ መሳካት ከእኛ የሚጠበቀው ለማበርከት ተግባራት በአደረጃጀት ለመስራት በእቅድ የሚመራ፣ በአግባቡ የተደራጀ፣ በፓርቲው እሳቤ የሚመራ፣ የፓርቲው እሳቤ የሚከተል፣ በቋሚነት የሚወያይ፣ በተግባር አፈፃፀም የሚመዘንና የሚመዝን የብልፅግና ፓርቲ የተግባርና በቃሉ የሚኖር አባል፣ አመራርና አደረጃጃት መፍጠር ነው፡፡ ብቁና ጠንካራ አደረጃጀት፤ ተዓማኒነት ያለው መረጃ ለብልፅግና ስኬት!!! | ||
![]() | ![]() | ![]() | ![]() |