admin
Fri, 01/03/2025 - 17:52
የማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ቅርጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊና የመንግስት ዋና ተጠሪ ዶ/ር ዲላሞ ኦቶሬ በፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ህልፈተ ህይወት የተሰማቸውን ሀዘን ገለጹ
ዶ/ር ዲላሞ ኦቶሬ ባስተላለፉት የሀዘን መግለጫ መልዕክት ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ በኢትዮጵያ የሰላማዊ ፖለቲካ ትግል ተምሳሌት የሆኑ ናቸው ብለዋል።
እስከ ህልፈተ ህይወታቸው ያላቸውን ሁሉ ለአገራቸው በመስጠት አገልግለዋል።
በህልፈተ ህይወታቸው የተሰማኝን ጥልቅ ሃዘን ልገልጽ እወዳለሁ ብለዋል።
ዶ/ር ዲላሞ ኦቶሬ ለቤተሰቦቻቸውና ወዳጅ ዘመዶቻቸው ለመላው ኢትዮጵያውያን መጽናናትን ተመኝተዋል።