Skip to main content
ኢትዮጵያ ያላትን ትልቅ የታሪክ ሐብት በሚያሰባስብ መልኩ በማጉላት ለአገር አንድነትና አብሮነት መጠቀም ይገባል - ዶ/ር ከይረዲን ተዘራ የሰላም ሚኒስትር ዴኤታ
በብልፅግና ፓርቲ ዋና ፅ/ቤት ‹‹የሃገር አንድነትና አብሮነትን የሚያፀና ትርክት›› በሚል ርዕስ የሰላም ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ከይረዲን ተዘራ ቃለ-ምልልስ አካሂደዋ፡፡
የኢትየጵያዉያን ልዩ መገለጫ እርስ በርሱ የተዛመደ፣ እጅጉን የተሳሰረና መነጣጠል የማይችል የጋራ ስነ-ልቦናዊ ዉቅር ያለዉ ሆኖ ሳለ ዘመናዊው የኢትዮጵያ ታሪክ፤ የተለያዩ ማንነቶችን ያስተናገደበት መንገድ ግን የሃገሪቱ የግጭት ታሪክ ማሳያ ተደርጎ እንዲወሰድ አድርጎታል ብለዋል፡፡
ብልፅግና ፓርቲ ሲመሰረት ታሳቢ ካደረጋቸዉ ጉዳዮች መካከል ሃገሪቱን ይህንን ከመሠሉ መሰረታዊ ችግሮች ማሻገር እንደነበር እንደሚያምኑ የገለፁት ዶ/ር ከይረዲን፤ ይህን የሃገረ መንግስት አመሰራረት ሂደት ስብራት መጠገንም ይገኝበታል ብለዋል፡፡
እንደ አድዋ የመሳሰሉ አኩሪ ታሪኮቻችንን በኩራት የምንናገረዉ በሃገረ መንግስቱ ዉስጥ ያሉ ማንነቶች በወራሪ ማንነቶች ባለመተካታቸዉ ትክክለኛ የነፃነት ትርጉም ከመሆኑ ባለፈ ታሪክን በሚገባው ልክ በመግለጽ ለአብሮነታችን መጠቀም እንደሚገባም ጠቅሰዋል፡፡
ብልፅግና ወጥና ሃገራዊ ፓርቲ ሆኖ ከተመሰረተ ጀምሮ ትኩረት በመስጠት የዳር ተብለዉ የተገፉ ህዝቦችን በሃገሪቱ የፖለቲካ ስልጣን ላይ እኩል ተሳታፊ እንዲሆኑ በማስቻል ለጋራ ሃገር ግንባታ ያለዉን ቁርጠኝነትም አስመስክሯል ያሉት የሰላም ሚኒስትር ዴኤታዉ ፓርቲዉ በባህሪዉ የትናንትን መልካም ነገር አክብሮ የሚወስድና ያለፈን የማያጠለሽ፤ ታላቁን ትርክት አጉልቶ በማስረፅ ቀጣዩን የሃገር ግንባታ ስራ እያሳለጠ ይገኛል ብለዋል፡፡
Image