Skip to main content
በመደመር እሳቤ ተግባራዊ የተደረጉ ስራዎች ወደ ጠንካራ የፖለቲካ፣የኢኮኖሚ እና ሌሎች ልዩ ልዩ የባህል እሴቶች መቀየር ተገቢ ነው - ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው
ሆሳዕና፣ታህሳስ 26/2017ዓ.ም
"ከቃል እስከ ባህል" በሚል መሪ ሀሳብ ክልል አቀፍ የከፍተኛ አመራሮች የግምገማ መድረክ መጠናቀቁን በማስመልከት የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ እንዳሻው ጣሰው ለመገናኛ ብዙሀን መግለጫ ሰጥተዋል።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ እንዳሻዉ ጣሰዉ እንደገለጹት ሀገራዊ ለውጡን ተከትሎ ልዩ ልዩ የልማት እና የመልካም አስተዳደር ስራዎች ተግባራዊ ሲደረግ ቆይቷል።
ከአንድ ሳምንት በፊት በሀገር አቀፍ ደረጃ የብልጽግና ስራ አስፈፃሚና የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት የባለፉትን ስድስት ዓመታት ጉዞ እና በአንደኛው የብልጽግና ፓርቲ ጉባኤ ላይ የተቀመጡ አቅጣጫዎች እንዲሁም የሁለተኛው ጉባኤ ዝግጅት ላይ ሰፊ ዉይይት መደረጉን ተናግረዋል።
በውይይቱ ያለፍንባቸው መንገዶች ያስመዘገብናቸው ውጤቶች እና ያጋጠሙ ችግሮች መገምገም ስለመቻሉ ክቡር ርዕሰ መስተዳድሩ አብራርተዋል።
ለሁለተኛው የብልጽግና ፓርቲ ጉባኤ ዝግጅት እስከ ታችኛው የመሰረታዊ ድርጅት ባለው መዋቅር አባላት ውይይት እንደሚያደርጉም አብራርተዋል።
ለውይይቱ የሀገር አቀፉን ሰነድ መነሻ በማድረግ አስፈላጊው የቅድመ ዝግጅት ስራ ስለመከናወኑ ነው ክቡር ርዕሰ መስተዳድሩ በመግለጫቸው ያመላከቱት።
ለውይይት የተዘጋጀው ሰነድ የክልሉን አጠቃላይ ፖለቲካዊ እንድምታ መሰረት ያደረገ ነው ያሉት ክቡር ርዕሰ መስተዳድሩ የከፍተኛ፣የመካከለኛ እና የጀማሪ አመራሩን አፈጻጸም መለካት የሚያስችል ግምገማ መደረጉን አውስተዋል።
" ከቃል ወደ ባህል" በሚል መሪ ሀሳብ የሚካሔደው የውይይት መድረክ እንድምታ ለውጡ ሲጀምር ሀሳብ ነበረ ያሉት ክቡር ርዕሰ መስተዳድሩ ይህም "ቃል "የመደመር እሳቤዎችን ማስገኘቱን ጠቁመዋል።
በመደመር እሳቤ ተግባራዊ የተደረጉ ስራዎች ወደ ጠንካራ የፖለቲካ፣የኢኮኖሚ እና ሌሎች ልዩ ልዩ የባህል እሴቶች መቀየር ተገቢ ስለመሆኑም ክቡር ርዕሰ መስተዳድሩ አጽንኦት ሰጥተዋል።
በክልሉ በሁሉም መዋቅር በክልል ደረጃ የተደረገው ግምገማ እንደሚካሔድ የተናገሩት ክቡር ርዕሰ መስተዳድሩ ከግምገማው ባለፈ የአመራር ምዘና እንደሚካሔድም ርዕሰ ክቡር መስተዳድሩ አመላክተዋል።
በስራው ጠንካራ በፖለቲካ አቅሙ የተሻለ የብልጽግናን አስተሳሰብ ባህል፣ እሴት እና መርሆዎች የተላበሰ አመራር መፍጠር ላይ በትኩረት እየተሰራ ነው ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ ለፓርቲው ጉባኤ የሚሳተፉ አባላትም በዚህ መመዘኛ የሚያልፉ መሆናቸውን አብራርተዋል።
በትላንትናው የግምገማ መድረክ ከስራ እና ከስነ ምግባር ጋር ተያይዞ የተስተዋሉ ጉድለቶችን ማረም የሚያስችል ግምገማ መካሔዱን ርዕሰ መስተዳድሩ ጠቁመዋል።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ ዶ/ር ዲላሞ ኦቶሬ እንደገለጹት ባለፉት ዓመታት በመንግስት እና በፓርቲ ስራዎች ላይ ያጋጠሙ ችግሮች እና የመፍትሄ ሀሳቦች ላይ ጥልቅ ውይይት መካሔዱን ተናግረዋል።
ባለፉት አመታት የፖለቲካ ስራዎች ስኬት በዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ ሂደት ላይ አዎንታዊ አስተዋጽኦ እንደነበረውም ዶ/ር ዲላሞ አብራርተዋል።
በክልሉ የፖለቲካ ምህዳርን የማስፋት ጉዳይ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶታል ያሉት ኃላፊው በዚህም የተመዘገበው ውጤት ስኬታማ እንደነበር አስታውሰዋል።
ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርም ከተደረገ ወዲህ በዘርፉ የታየው ለውጥ ውጤታማ ነው ያሉት ኃላፊው ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ ረገድ ያለውን ሚናም ዶ/ር ዲላሞ በአብነት ጠቅሰዋል።
በክልሉ የሌማት ትሩፋት፣የበጋ ስንዴ፣የአረንጓዴ አሻራ እንዲሁም በቅመማ ቅመም ዘርፍ ደግሞ የኤክስፖርት ምርቶች ላይ የተገኘው ለውጥ አበረታች ስለመሆኑም ዶ/ር ዲላሞ አስረድተዋል።
የተገኙ ስኬቶች የመኖራቸውን ያህል አመራሩ በአመለካከት እና በተግባር አንድ ሆኖ ከመውጣት አንጻር ክፍተት እንዳለ በውይይት መድረኩ መለየት ስለመቻሉም ዶ/ር ዲላሞ አብራርተዋል።
አመራሩ ያሉበትን ጉድለቶች አርሞ ሀገር እና ህዝብን መለወጥ የሚችልበትን ስርዓት መዘርጋት ተገቢ ስለመሆኑም ጠቁመዋል።
Image