admin
Tue, 12/17/2024 - 18:44
ብቃትና ጥራት ያለው ጠንካራ አደረጃጀት እንዲፈጠር ጠንካራ የአደረጃጀት መሪ አስፈላጊ ነው፦ አቶ ይግለጡ አብዛ
ሆሳዕና ታህሳስ 07/2017ዓ.ም
የማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ይግለጡ አብዛ የዘርፉን የእስከአሁን የተግባር አፈፃፀም ገምግመዋል።
በግምገማ መድረኩ ላይ አቶ ይግለጡ ብቃትና ጥራት ያለው ጠንካራ አደረጃጀት እንዲፈጠር ጠንካራ የአደረጃጀት መሪ አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል።
በ2017 በጀት አመት በአደረጃጀት ዘርፍ በርካታ ስራዎች እንደተሰሩ አቶ ይግለጡ ገልፀው በተለይም አደረጃጀትን መልሶ የማደራጀት፣ የማጥራት እና የመለየት ስራዎች ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባም አሳስበዋል።
በተጨማሪም በመመሪያዎች፣ በፓርቲ ፕሮግራምና መተዳደሪያ ደንብ ላይ ግንዛቤ የማስጨበጥ ስራ መሰራቱንም ጨምረው ገልፀዋል::
በየደረጃው የሚካሄዱ የህዋሳት ውይይቶች በየተቋማቸው የሚነሱ የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ካሉ በዚያ በጥልቀት በመምከር የመፍትሄ ሀሳብ እስከማምጣት ድረስ ትግል ማድረግ እንደሚገባ አቶ ይግለጡ በአጽንኦት አሳስበዋል።
ስነ ምግባር ላይ በዋናነት ችግር አባባሽ ጉዳይ ነጠላ ትርክት ነው ያሉት አቶ ይግለጡ ከፋፋይ እና የሚለያይ ትርክት አገር አፍራሽ መሆኑን መገንዘብ መታገልና ታላቁን አሰባሳቢ የወል ትርክት መገንባት ተገቢ መሆኑን ጠቁመዋል።
ሀገር ከተረጂነት እና ከልመና መላቀቅ ጊዜ የማይሰጥ ጉዳይ መሆኑን በመረዳት ከተረጂነት አስተሳሰብ ለመላቀቅ በህዋሳት በሚኖሩ ውይይቶች አባላት በቁርጠኝነት በመነሳት ራሱ ቅድሚያ ተለውጦ ለሌላው እስኪተርፍ ግንዛቤ መመፍጠር እንደሚያስፈልግ አቶ ይግለጡ ገልጸዋል።
የፓርቲውን በጠንካራ አባላት የማጠናከር ስራ በመስራት የአባላት ምልመላ እንደተደረገና ተተኪ አመራሮችን በመለየት የማዘጋጀት ስራም እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል::
ጠንካራ የፓርቲ ተቋማዊ አደረጃጀት ለመፍጠር በአደረጃጀትና አሰራር መመሪያ መሰረት አደረጃጀቶችንና ኮሚቴዎች ለማደራጀት ጥረት መደረጉ፣በክላስተሮች መረጃ የማደራጀት ኃላፊነት በአደረጃጀት በኩል ተጠናክሮ እየተሰራ መሆኑ በጥንካሬ ተገልጿል።
ከክልል ማዕከል ጀምሮ በሁሉም ደረጃ የመ/ድርጅት አመራር በወጣበት የመተካትና መልሶ የማደራጀት ሥራ ተቋም የማስቀጠል በአብዛኛው መዋቅር የተሻለ መሆኑ ተመላክቷል።
በመድረኩ የዞኖች፣የልዩ ወረዳዎች የቅ/ጽ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊዎች የክልል ማዕከላት የመሰረታዊ ድርጅት የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊዎች ተሳትፈዋል።
Image
