admin
Tue, 12/17/2024 - 18:30
ሆሳዕና፤ታህሳስ፣01/2017ዓ.ም
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ክቡር አቶ እንዳሻው ጣሰው በምክክር መድረክ እንዳሉት የብልፅግና ጉዞ በፈርጅ ብዙ እንቅስቃሴ ውስጥ ማለፍ አለበት ብልጽግናን ለማረጋገጥ በተሟላ መንገድ እያቀድን እጅግ በጣም ሰፋፊ ስራዎችን መስራት ይጠበቅብናል።
የገቢ ሥራ እና የሥራ ዕድል ፈጠራ በክልላችን የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ናቸው። ገቢ ከሌለ የምናስባቸውን የልማት ስራዎች ማሳለጥ አንችል፤ የስራ እድል ፈጠራ ከሌለም ከተለያዩ የትምህርት ተቋማት ተመርቀው ለወጡት እንዲሁም የአርሶአደር ልጆችን ጥያቄ መመለስ ይከብዳል። ከዚህ መነሻ ሁለቱም ዘርፎች እስከአሁን በተመሩበትን ሂደት ያሉ ጥንካሬዎችንና ጉድለቶችን በመለየት የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ሊሰሩ ይገባል።
ተረጂነት ለብዙ ጊዜ አቅሞቻችንን ሳናሰባስብ በቀረንበት ወቅት የተጠቀምነው ጉዳይ ነው ያሉት ክቡር ርዕሰ መስተዳድሩ አሁን ከተረጂነት መውጣት እንዳለብን ምርታማ መሆን አስፈላጊ መሆኑን ብልጽግና አምኖ ከተረጂነት ወደ ምርታማነት ለምናደርገው ጉዞ በየደረጃው የአመለካትና የተግባር ትግል በማድረግ በትኩረት ሊሰራ ይገባል፤
ከተሞቻችንን ከማዘመን አኳያ በተለይ የኮሊደር ልማት እስከአሁን ዝግጅት ስናደረግ የቆየን ቢሆንም በተወሰኑ ከተሞች ጥሩ ጅምሮች አሉ ብለዋል።
በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በከፍተኛ አመራሮች ስልጠና ማጠቃለያ በነበረው መድረክ 'አንድ ፕሮጀክት በአንድ ከተማ' እንዲሰራ አቅጣጫ ማስቀመጣቸውን ያስታወሱት ክቡር ርዕሰ መስተዳድሩ በዚህም በክልላችን ከ80 በላይ ኘሮጀክቶች መቀረጻቸውን አስታውቀዋል።
ርዕሰ መስተዳድሩ በሰባቱም የክልል ማዕከላት የቢሮ ግንባታ በጥር ወር እንደሚጀመር ጠቁመው ይህም 6 ቢሊዮን ብር የሚፈጅ ሲሆን የግንባታ እድሜው ከሁለት እስከ አራት አመት መሆኑን አስታውቀዋል።
በየደረጃው በተሰጡ የአመራርና የአባላት የአቅም ግንባታ ስልጠናና አጠቃላይ የክልሉ ፖለቲካዊ ሁኔታ በተለይም ከብልጽግና አቋም በተጻራሪ የመቆም ብልሽቶች የት አከባቢ በማን እየተፈጸመ እንዳለ እያጠራንና እየቀረፍን እንሄዳለን።
የጠራ አመለካከት ያለመያዝ ብልጽግናዊ አመለካከት ይዞ በዚህ አመለካከት ስራን አለመምራት በስራ ቦታ ሙሉ ሰዓትን ያለማሳለፍ በሌሎች ልዩ ልዩ ነገሮች መጠመድ የሚታዩ ቦታዎች መኖራቸውን ያነሱት ክቡር ርዕሰ መስተዳድሩ ለኢትዮጲያ ሆነ ለማዕከላዊ ኢትዮጵያም ስለማይጠቅም ሁሉም ከዚህ ተግባር ታርሞ የተጣለባትን ኃላፊነት በታማኝነት እንዲወጣ አሳስበዋል።
Image
