admin
Mon, 12/16/2024 - 15:55
የብልጽግና ፓርቲ የኢንስፔክሽንና ስነ-ምግባር ኮሚሽን በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት ተገኝተው እስከአሁን የነበረውን የኮሚሽኑን የስራ ሂደት በመመልከት ድጋፍ አድርገዋል።
ሆሳዕና፤ታህሳስ፣05/2017ዓ.ም
የክልሉ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የፓለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ይሁን አሰፋ የፌዴራሉ የኢንስፔክሽንና ስነ-ምግባር ኮሚሽን ዋና ጽ/ቤት ያደረገውን ድጋፋዊ ክትትል በማድነቅ የክልሉ ኢንስፔክሽንና ስነ-ምግባር ኮሚሽን ሁሉም መዋቅሮች ያሉበትን ደረጃ በአግባቡ በመለየት፣ ድጋፋዊ ክትትል በማድረግና ግንባታ በመስጠት ወደ ተቀራራቢ ደረጃ በማምጣት የተቋሙን የመፈፀምና የማስፈፀም አቅም ለማሳደግ በትኩረት እየሰራ ነው ብለዋል።
ኮሚሽኑ ተጠናክሮ ሚናውን እንዲወጣና ፓርቲው የያዛቸው ህዝባዊ ተጠቃሚነት እና ሁለንተናዊ ብልፅግና የማረጋገጥ ዓላማዎች ግባቸውን እንዲመቱ በፓርቲው መተዳደሪያ ደንብ የተሰጠውን ሀላፊነት እንዲወጣ በየደረጃው ያሉ ሁሉም መዋቅሮች የተጣለባቸውን ሃላፊነት በታላቅ ቁርጠኝነት እየፈፀሙ መሆኑንም አቶ ይሁን አክለው ገልፀዋል።
አቶ ሀብታሙ ሲሳይ የብልጽግና ፓርቲ ኢንስፔክሽንና ስነ-ምግባር ኮሚሽን ዋና ፅ/ቤት ሀላፊ በክልሉ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የኢንስፔክሽንና ስነ-ምግባር ኮሚሽንም ቅ/ጽ/ቤት የተሰሩ ስራዎችን በጥልቀት ምልከታ በማድረግ በሰጡት ግብረ-መልስ ላይ እንደተናገሩት የክልሉ ኮሚሽኑ ከተቋቋመ አንድ ዓመት ቢሆንም ጠንካራ ስራዎችን እየሰራ ያለ ቢሆንም በክፍተት የታዩ ተግባራቶችን በትኩረት ይዞ ማረም እንደሚገባ እንዲሁም ጥንካሬዎችን ደግሞ ይበልጥ በማጉላት ለቀጣይ ግብዓት ማድረግ ይገባል ብለዋል።
አቶ ሀብታሙ አያይዘዉም እንደተናገሩት የፓርቲው ገንዘብ ንብረትና ሰነዶች በአግባቡ መያዛቸውንና ሥራ ላይ መዋላቸውን መቆጣጠርና የአባላት መዋጮ በትክክል በስኬል መሰረት ተሰብስቦ ገቢ መደረጉን ማረጋገጥ የተሰራዉን ሥራ ጠንካራ ሀገርና ፓርቲ ለመገንባት የሚደረገዉን ጥረት የሚያግዝ መሆኑን ተናግረዋል።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ኢንስፔክሽንና ስነ- ምግባር ኮሚሽን ቅ/ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ አብዱልዋሪስ ጀማል የኮሚሽኑ አደረጃጀት ብቁ ሆኖ በፓርቲው መተዳደሪያ ደንብ የተሰጡትን ተልእኮ ለማሳካት የተሰሩ ተግባራትን ያቀረቡ ሲሆን ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ ሰጥተዋል ።
Image
