የሴቶች ክንፍ መሪ ወ/ሮ ኤልሳቤጥ ሽመልስ መልዕክት

የሴቶች ክንፍ መሪ መልዕክት
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ክንፍ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የብልጽግና ፓርቲ ክንፍ በመሆን የከተማዉ ሴቶች የወቅቱን መድረክና ተልእኮ ተገንዝበዉ በብቃት የመፈጸም ፤ ህብረተሰባዊ ለዉጥን የማፋጠን ፤የከተማችን ሴቶች በጋራ አላማቸዉ ዙሪያ የማሰለፍና የትግል መድረክ በመሆን ጥቅሞችን የማጣጣም ቁልፍና ወሳኝ ተልኮ ይዞ የተቋቋመ የሴቶች የፖለቲካ አደረጃጀት
ክንፉ ሴቶች በከተማችን በሚካሄደዉ ልማት ንቁ ተሳታፊና ከሚገኘዉም የኢኮኖሚ እድገት ተጠቃሚ መሆናቸዉን ማረጋገጥ የሴቶችን ማህበራዊ ተሳትፎ እና ተጠቃሚነት እንዲሁም ሴቶችን ዝቅ አድርገዉ የሚመለከቱ አስተሳሰቦችንና ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን እና ሴቶች የራሳቸዉን የዝቅተኝነትና የበታችነት አመለካከት ማስወገድ፤ በየደረጃዉ እኩል የፖለቲካ ተሳትፎና የዉሳኔ ሰጭነት ስልጣን እንዲኖራቸዉ በዲሞክራሲያዊ ስርአት በህገመንግስቱ እንዲሁም በሀገራዊ ምክክር መድረክ ዘላቂ ተሳትፎና አስተዋጽኦ በማድረግ የተጀመረዉን የብልጽግና ጉዞ በማፋጠን ተጠቃሚነታቸዉን ማረጋገጥና የከተማችንን ብሎም የሀገራችንን መጻኢ ግዜ ብሩህ ማደረግ ይጠበቃል፡፡፡፡
የሴቶች ክንፍ መሪ ወ/ሮ ኤልሳቤጥ ሽመልስ
አመሰግናለው!